ካሲናው ጎጃም | አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video)ካሲናው ጎጃም
______________
ግጥም: አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ሐይለ እየሱስ ደርብ የህዝብ
ዜማ: የህዝብ ዋሽንት: አይችሉህም መንግስቴ
ከበሮ: ሐገረሰላም ሻፊ
መሰንቆ: እንድሪስ ሐሰን አረሒት : እየሩስ መለሰ
አድማቂ: መላኩ ታረቀኝ
ተቀባይ: አማኑኤል አሊ: አሳየ ፈንቴ: ክንፈገብርኤል ክንዱ :ተፈሪ አሰፋ
ጋፈርና ግሪፕ: አበበ ከፈለኝ፣ ዳግማው አበበ
ረዳት ካሜራ: የአብስራ ደሳለኝ
ፕሮዳክሽን ዲዛይነር: ሄለን ብዙነህ
ፕሮዳክሽን አስተባባሪ: አከለ መሰለ
ፕሮዳክሽን ማናጀር: ዮናስ አብርሀም
ሲኒማቶግራፈር: ፍስሀፅዮን ንብረት
ከለር: ሮሀ ስቱዲዬ
ኤዲተርና ዳይሬክተር: ሰውመሆን ይስማው
ፕሮዲዩሰር: ብርቧክስ ሪከርድስ
———————-
ልዩ ምስጋና
ለዲማ እና አካባቢው ነዋሪዎች
ግንቦት 4/2015 ዓ/ም
——————–

ካሲናው ጎጃም ግጥም
—————————-
መላየ ነይ መላ አለው መላ መላ (3)
አቴ መላ ዘውዴ ዘውዴ (3)
የአንችው ማሽላ ነው ዘውዴ
የእኔ አዝመራ ስንዴ ዘውዴ
እቴ መላ ዘውዴ
ሐገራችን ጎጃም ዘወዴ (ወንዛችን አባይ)2
እንደመስቀሏ ወፍ ዘውዴ (ብቅ አትይም ወይ)
ግምባሯን ቶ መስቀል ዘወዴ (የተነቀሰችው )2
ያያ ወንድአለን ልጅ ዘውዴ (ነብሮን አገባችው
የዳጉሳ ጠላ የለውም ዘውዴ( የለውም ቅራሪ)
አሁን ገና መጣች ዘውዴ (አስኳላ ተማሪ)2
ዳማይ አንችን ነው ዳማየ (2)
እናት ወልዳ ወልዳ ዳማየ
ስም ማውጣት ታውቃለች ዳማየ
የመጀመሪያውን ዳማየ
በላይ ትለዋለች ዳማየ
ደግሞም አስቀጥላ ዳማየ
ሽፈራው ትላለች ዳማየ
ደሞም አስቀጥላ ዳማየ
ባንችዋ ትላለች ዳማየ
የማሳረጊያዋን ዳማየ
ይጋርዱሽ ትላለች ዳማየ
ዳማይ አንችን ነው ዳማየ (2)
ሎሚተራ ተራ ዎ (4)
እናቴን አደራ
አሸበል ገዳየ አሐው ገዳየ
አይናማው ገዳየ አሐው ገዳየ
ሻየ ገዳየ አሐው ገዳየ
አታሞው ሲመታ አሐው ገዳየ
መሬቱ አረገደ አሐው ገዳየ (2)
ያያ ኩታ ለብሶ አሐው ገዳየ
ዝናብ አወረደ አሐው ገዳየ(2)
ድግሱ አማረላት አሐው ገዳየ
እመ ተመናሸች አሐው ገዳየ
ታተይ ተመናሸች አሐው ገዳየ
መቀነቷን ታትቃ አሐው ገዳየ
ዋንጫ ለቀለቀች አሐው ገዳየ(2)
ያዋልዳል በሬ( ያዋልዳል ላም)2
የእናጅሬው አገር እንዴት ነው ጎጃም
ድግሱን ደግሶ( አይነግርም አዋጅ)2
መንገደኛው ሁሉ ሰተት ነው እንጅ
ምንኛ ደግ ነው( የእዜሩ በረከት)2
በውሀም አይደለ በቅምጫና ወተት
ጋኑን እጠኝና (በጋምቢሎ ጭስ)2
በጥብጠሽ ጠብቂኝ ገምበሀ ስደርስ
ኩራትሽ (5)ራትሽ
ዶቅማ መቅመስሽን አወቅሁ በምላስሽ
ደልቂ (6)
እኔ እያለሁልሽ እንደ ፀሐይ ሳቂ
ደልቂ(6)
አማቶችሽ ዘንዳ መጠሽ ተመረቂ
ያለ ዛሬ ቤቴን (አታውቀውም ብሎ)2
ጠሪ አክባሪ ድሷል አቆልቋይ አክሎ
ባለጌታው ባይሸሽ አብየ ሰንደቁ አርበኛው ሰንደቁ
ገና እንደፎከረ ጠላጦች ወደቁ
ፍጥረት መጀመሪያው የአፍላጋት መፍለቂያ
የዬቶር ሞገድ
ካሲናው ጎጃም ነው ምድሪቱ ምጣድ
ደልቂ (6)
ከሽማግሌ እግር ወድቀሽ ተመረቂ
ደልቂ (6)
እኔ እያለሁልሽ እንደ ፀሐይ ሳቂ
—————————
ካሲናው ጎጃም | አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video)
—————————
#kasinawugojam
————————–
Check Out New Ethiopian Entertainment Videos
by Subscribing @Birbaux Records.

#BirbauxRecords. #SewMehonFilms #EthiopianMusic #gonder

unauthorized use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited

Copyright ©Birbaux Records. SewMehon Films

source

Comments are closed.

Scroll to Top